Logo
^

Share

Dilla university graduated students trained in the field of health

  • Dilla university graduated students trained in the field of health

ዲላ ዩኒቨርሲቲ በጤና ዘርፍ እና በተለያዩ የትምህርት መስኮች ያሰለጠናቸውን ተማሪዎች አስመረቀ

ዲ.ዩ:- ሕዳር 10/2015 ዓ.ም (ህ.ዓ.ግ) የዲላ ዩኒቨርሲቲ ህክምና እና ጤና ሳይንስ ኮሌጅ በተለያዩ የጤና ዘርፎች ያሰለጠናቸውን ተማሪዎች አስመርቋል። 

ዛሬ በዋናው ግቢ ሁለገብ አዳራሽ በተካሄደው የምርቃት ስነ-ስርአት ከህክምና እና ጤና ሳይንስ ኮሌጁ ምሩቃን በተጨማሪ በዩኒቨርሲቲው በልዩ ልዩ የትምህርት መስኮች ተማሪዎች የሰለጠኑ ተማሪዎችም ተመርቀዋል።

በዲላ ዩኒቨርሲቲ የአስተዳደር እና ተማሪዎች አገልግሎት ምክትል ፕሬዝዳንት ዶ/ር ዳዊት ሀዬሶ "እንደ ሀገር በርካታ ተግዳሮቶች፤ ኮቪድ-19፣ የሀገራችን አለመረጋጋት፣ የውጭ ሀይሎች ጣልቃ ገብነት እና ሌሎች መሰል ችግሮችን ተቋቁመን ያለፍንበት ጊዜ መሆኑ እና ይህን ተቋቁማችሁ መመረቃችሁ ልዩ ያደርገዋል" ብለዋል።

ዶ/ር ዳዊት በመክፈቻ ንግግራቸው ተመራቂዎች አንደኛው ምዕራፍ በስኬት አጠናቅቀው ለዚህ ክብር በመብቃታቸው "እንኳን ደስ አላችሁ" ነው ያሉት። ዶ/ር ዳዊት አክለውም ተመራቂዎች የዩኒቨርሲቲው አልሙናይ ሆነው ቤተሰብነታቸው እንደሚቀጥል ገልፀው "ዩኒቨርስቲውም በቅርበት ስራዎችን አብሯቸው ይሰራል" ብለዋል።

የእለቱ የክብር እንግዳ የደቡብ/ብ/ብ/ሕ/ክ/መንግስት የጤና ቢሮ ምክትል ሀላፊ እና የሕክምና አገልግሎት ዋና ዳይሬክተር አቶ ናፍቆት ብርሃኑ ለተመራቂዎች የስራ መመሪያ ሰጥተዋል። አቶ ናፍቆት በንግግራቸው የጤና ሙያ ልዩ የሚያደርገው ከክቡር የሰው ልጅ ህይወት ጋር በቀጥታ የተቆራኘ መሆኑ ነው ብለዋል።  

ተመራቂዎች ይህንን ተገንዝበው ሙያው በሚያዘው መሰረት የጾታ፣ ዘር፣ ሀይማኖት፣ ሀብት እና ሌሎች ልዩነቶችን በማስወገድ የሰው ልጅን ከሕመሙ ለመፈወስ የሚችሉትን ሁሉ እንዲያደርጉ መመሪያ አስተላልፈዋል።

የዲላ ዩኒቨርሲቲ የሬጅስትራርና አሉምናይ ዳይሬክተር አቶ ኢሳያስ ይልማ በበኩላቸው በዛሬው እለት በመጀመሪያ ዲግሪ ሁለት መቶ ሃያ (220)፣ በሁለተኛ ዲግሪ እስራ ዘጠኝ (19) በአጠቃላይ 229 ተማሪዎች በሕክምና ላብራቶሪ፣ ሕብረተሰብ ጤና አጠባበቅ፣ አንስቴዥያ፣ ፋርማሲ፣ ሚድዋይፍሪ እና ሳይካትሪ መመረቃቸውን አሳውቀዋል።

በተጨማሪም በሌሎች ኮሌጆች በመደበኛ፣ በክረምት፣ በቅዳሜ እና እሁድ መርሃግብር የተማሩትን አራት ሺህ ስድስት መቶ አስራ አምስት (4615) ተማሪዎች መመረቃቸውን ገልጸዋል።

ከህክምና እና ጤና ሳይንስ ኮሌጅ ከፍተኛ ውጤት ያመጣችው የሕብረተሰብ ጤና አጠባበቅ ምሩቅ ኢክራም ጀማል አራት ነጥብ (4.00) በማምጣት የወርቅ ሜዳሊያ ተሸላሚ ሁናለች። 

ተመራቂዋ "ይህን ውጤት እንዳስመዘግብ እገዛ ላደረጉልኝ ቤተሰቦቼ፣ መምህራንና ጓደኞቼ አመሰግናለሁ" ስትል ደስታዋን ለህዝብና ዓለምአቀፍ ግንኙነት ዳይሬክቶሬት ሪፖርተር አጋርታዋለች።

በእለቱ የክብር እንግዶች፣ የዩኒቨርስቲው ከፍተኛ አመራር አባላት፣ የተመራቂ ቤተሰቦች እና ባለ ድርሻ አካላት የተገኙ ሲሆን የዲላ ዩኒቨርሲቲ የባህል ማዕከል ልዩ ልዩ ጥዑም ዜማዎችን በማቅረብ ዝግጅቱን አድምቆታል።

የምርቃት ስነ ስርአቱ የህክምና እና ጤና ሳይንስ ኮሌጅ ተመራቂዎች በልዩ ልዩ ሙያዎች እንደሚገባ ሙያዊ ቃለ-ምህላ በመፈፀም ተጠናቋል።